በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሞቅዲሾ በተጠመዱ ፈንጂዎች ሥድስት ሰዎች ሕይወታቸው አለፈ

ዛሬ፣ ሶማልያ ዋና ከተማ ሞቅዲሾ ውስጥ በሚገኘው የፕሬዚዳንቱ ቤተ መንግሥት አጠገብ የደረሱ ሁለት መኪና ላይ የተጠመዱ ፈንጂዎች፣ አምስቱን አጥቂዎች ጨምሮ በጠቅላላው ሥድስት ሰዎች መሞታቸውን፣ የአይን ምስካሪዎች አስታወቁ።

ዛሬ፣ ሶማልያ ዋና ከተማ ሞቅዲሾ ውስጥ በሚገኘው የፕሬዚዳንቱ ቤተ መንግሥት አጠገብ የደረሱ ሁለት መኪና ላይ የተጠመዱ ፈንጂዎች፣ አምስቱን አጥቂዎች ጨምሮ በጠቅላላው ሥድስት ሰዎች መሞታቸውን፣ የአይን ምስካሪዎች አስታወቁ።

አካባቢው በነበሩ ምስክሮች ገለጣ መሠረት፣ በፍጥነት ትነዳ የነበረች መክና፣ ፒስ ጋርደን በተባለው መናፈሻ ሥፍራ ስትደርስ ፍንዳታ በማድረሷ፣ በፀጥታ አስከባሪዎችና በታጣቂዎቸ መካከል ከባድ የተኩስ ልውውጥ ተካሂዷል።

በዚህ ጥቃት፣ በሌሎች ተጨማሪ ሰዎቸ ላይ የመቁሰል አደጋ እንደደረሰና፣ ቁስለኞቹ ወደ ሐኪም ቤት መወሰዳቸውንም አንድ የዐይን ምስክር ለቪኦኤ ሶማልኛ አልግሎት አስታውቋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG