ድርጅቱ ከተቋቋመ አሥራ አንድ ዓመታት የሆኑትና በዩናይትድ ስቴትስና በአውሮፓ፣ እንዲሁም በሌሎች አካባቢዎች 28 ሺህ የኢንተርኔት አባላት ያሉት መሆኑ ተገልጿል፡፡
ሕዝብ ለሕዝብ በተለይ በጤናው ዘርፍ በሃገር ውስጥ ላሉ ተቋማት ድጋፍ የሚሰጡ የሕክምና ባለሙያዎች ይሣተፉበታል፡፡
ኢትዮጵያ ባላት አቅም እና የሰው ጉልበት ትልቅ እርዳታ የሚያስፈልጋት ሃገር በመሆኗ ባለሙያዎች እየተመላለሱ ሕዝባቸውን ማገልገል እንዳለባቸው በሃዋርድ ዩኒቨርሲቲ የሕዝብ ጤና አጠባበቅ ተባባሪ ፕሮፌሰሩ ዶ/ር አሕመድ ሞኤን ይመክራሉ፡፡ ለዝርዝሩ ዘገባውን ያዳምጡ፡፡