በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኮሮናቫይረስ ክትባት


በዓለም ዙሪያ በኮሮናቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠው ሰዎች ቁጥር 14,739,450 ሲሆን በበሽታው ሳቢያ ህይወታቸውን ያጡት 610,776 መድረሳቸውን የጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ የኮቪድ-19 መረጃ ማዕከል መረጃ ይጠቁማል።

ቫይረሱን ለመከላከል የሚውል ክትባት ፍለጋ ላይ ያሉት ተመራማሪዎች መልካም እርምጃ እያዩ መሆናቸውን እየተናገሩ ናቸው። የብሪታንያው ኦክስፈርድ ዩኒቨርስቲና የብሪታንያና ስዊድን መድሃኒት ኩባኒያ አስትራዜኔካ በጋራ የቀመሙት ክትባት አንዱ ሲሆን ሌላው ደግሞ ካንሳይኖ የተባለው የቻይና ባዮቴክ ኩባኒያ የሰሯቸው ክትባቶች በሰው ላይ በተደረጉ ጠንካራ ውጤት ማሳየታቸውን ዘ ላንሴት መጽሄት ላይ የወጡ የባለሙያ ግምገማዎች አመልክተዋል።

የዩናይትድ ስቴትሱ የመድሃኒት ኩባኒያ ፋይዘር እና የጀርመኑ ባዮቲክ በህብረት የቀመሙት ክትባት ጥሩ ውጤት ማስመዝገቡን ትናንት አስታውቀዋል። በተለይ ትልቁን ትኩረት የሳበው የኦክስፈርድና የአስትራዜኔካው ዜና ሲሆን የዚህ ምክንያቱ ኩባኒያው ፍቱን እና ጉዳት የማያስከትል ክትባት ማግኘት ከቻለና የቁጥጥር መስፈርቶችን ማለፍ ከቻለ ክትባቶቹን አምርቶ ሊያቀርብ ከበርካታ መንግሥታት ጋር ውል ተፈራርሟል።

ኒው ዮርክ ታይምስ እንደዘገበው ክትባቱ ብሪታንያ ብራዚል እና ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ከአስር ሽህ ለሚበልጡ በጎ ፈቃደኛ የሙከራው ተሳታፊዎች ተሰጥቷል።

በሚቀጥለው ሳምንት ደግሞ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ለሠላሳ ሽህ በጎ ፈቃደኞች ይሰጣል።

XS
SM
MD
LG