በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“ሱዳን ውስጥ ከ 1 ሚሊዮን በላይ የፖሊዮ ክትባት ወደመ” ዩኒሴፍ


ሱዳን ውስጥ እየተካሄደ ካለው ውጊያ ተያይዞ በደረሰ ዝርፊያ ከ1 ሚሊዮን የሚበልጡ የፖሊዮ ክትባቶች መውደማቸውን የተባበሩት መንግሥታት የሕጻናት መርጃ ድርጅት አስታወቀ፡፡

የዩኒሴፍ የአጣዳፊ መርሐ ግብሮች ምክትል ዳይሬክተር ሄዝል ዴ ዌት ባለፈው ዐርብ በሰጡት መግለጫ ደቡባዊ ዳርፉር ውስጥ ያሉ ባለማቀዝቀዣ የክትባት ማከማቻዎች መዘረፋቸውን ወይም መውደማቸውን ገልጸዋል፡፡

ዩኒሴፍ እአአ ባለፈው 2022 ዐመተ ምህረት መጨረሻ ላይ የተቀሰቀሰውን የፖሊዮ ወረርሺኝ ተከትሎ ተከታታይ የክትባት ዘመቻዎችን በማካሄድ ላይ እንደነበረ ተጠቁሟል፡፡

XS
SM
MD
LG