በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፖላንድ - ጀርመን ሰር ‘ሊዮፓርድ - ሁለት’ ታንኮችን ለዩክሬይን ለመላክ እየተዘጋጀች ነው


ፎቶ ፋይል፦ የጀርመን ቻንስለር ኦላፍ ሾልዝ ጀርመን በሚገኝ የጀርመን ጦር መንደር በጎበኙ ወቅት እአአ 11/17/2023
ፎቶ ፋይል፦ የጀርመን ቻንስለር ኦላፍ ሾልዝ ጀርመን በሚገኝ የጀርመን ጦር መንደር በጎበኙ ወቅት እአአ 11/17/2023

በርሊን ወደ ዩክሬይን የመላካቸው ዕጣ እያነጋገረ ያሉትን ሊዮፓርድ ሁለት የተባሉትን ጀርመን ሰር ታንኮች አስመልክቶ ቀጥተኛ ፍቃድ ባትሰጥም አገራቸው ያን ማድረግ የሚያስችላትን የአገሮች ሕብረት በማሰባሰብ ላይ መሆኗን የፖላንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ሞቴየሽ ሞርቪየንስኪ ዛሬ ሰኞ ለጋዜጠኞች በሰጡት ቃል “ፖላንድ የጀርመንን ፈቃድ ትጠይቃለች። ሆኖም ግን የበርሊንን ይሁንታ መጠየቅ አስፈላጊነት ሁለተኛ ላይ የሚመጣ ነው” ብለዋል።

ሞርቪየንስኪ አክለውም “ሊዮፓርድ ታንኮቹ ለዩክሬይን ይላኩ ዘንድ በበርሊን መንግሥት ላይ ሳናቋርጥ ግፊት እናደርጋለን” ማለታቸው ተዘግቧል።

የጀርመኗ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አናሊና ቤርቦክህ ለፈረንሳዩ ኤልሲይ የቴሌቭዥን ጣቢያ ትናንት እሁድ ሲናገሩ ፖላንድ የሊዮፓርድ 2 ታንኮችን ወደ ዩክሬን ለመላክ ፍቃድ ብትጠይቅ ሃገራቸው “መንገድ አትዘጋባትም” ብለዋል።

ቤርቦክህ ይህን አስተያየት እስከ ሰጡበት ጊዜ ድረስ፣ ጀርመን የተባሉትን ታንኮች ራሷም ሆነ ካሁን ቀደም ከጀርመን የገዙ አገሮች

ወደ ዩክሬን እንዲልኩ ትፈቅድ እንደሆን ፍንጭ ከመስጠት ተቆጥባ ቆይታለች።

XS
SM
MD
LG