የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪ ቢሮ ኃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ዛሬ ከሰዓት በኋላ መግለጫ በሰጡበት ወቅት ነው ይህን የገለፁት።
በመግለጫቸው ላይ በወቅቱ በነበረው ግጭት የ 78 ዜጎች ህይወት ማለፉን ጠቁመዋል።
በወቅቱ በግጭቱ ሊደርስ የሚችለውን ጉዳት ለመቀነስ የፀጥታ መዋቅሩ በሙሉ አቅሙ መስራቱንም ገልጸዋል።
ቀውሱን ለማርገብ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶች እና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ላደረጉት አስተዋፀዖ መንግሥት ምስጋና አቀርቧል።
ግጭቱ የተነሳው በአክቲቪስቱ ጁዋር ሞሐመድ ላይ በተደረገ አያያዝ ምክንያት በተነሳ ተቃውሞ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ቃል-አቀባይ ቢልለኔ ስዩም መግለፃቸውን ሮይተርስ የዜና አገልግሎት ጠቅሷል።
በሀገሪቱ ባለፈው አንድ ዓመት ተኩል ጊዜ ውስጥ በተፈጠሩ ተመሳሳይ ግጭቶች ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር ከዋሉት 33 ሺህ 221 ግለሰቦች መካከል ከ2 ሺህ በላይ ለህግ መቅረባቸውን አቶ ንጉሱ ጥላሁን ተናግርዋል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ