በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ 400 ሺሕ ሰዎች ተፈናቀሉ


የመንግሥታቱ ድርጅት ጦር ከጎማ ውጭ በኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ፤ እአአ ጥር 24/2025
የመንግሥታቱ ድርጅት ጦር ከጎማ ውጭ በኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ፤ እአአ ጥር 24/2025

በኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ባለው ሁከት ምክንያት 400ሺሕ ሰዎች ተፈናቅለዋል ሲል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዛሬ ዓርብ አስታውቋል።

በሩዋንዳ እንደሚደገፍ የሚነገረውና ኤም 23 የተሰኘው ቡድን ከኮንጎ ሠራዊት ጋራ በመፋለም ላይ ሲሆን፣ የሃገሪቱ የሰሜን ኪቩ ግዛት መዲና በሆነችው ጎማ አካባቢ ያለውን ቁጥጥር በማጥበቅ ላይ መሆኑ ተነግሯል።

በምሥራቅ የሃገሪቱ ክፍል የሚገኙ ሲቪሎችና የሃገር ውስጥ ተፈናቃዮች ሁኔታ እንደሚያሳስበው የተመድ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን አስታውቋል።

ኮሚሽኑ በተጨማሪም ሁሉም ወገኖች ሲቪሎችን ከአደጋ እንዲጠብቁ፣ የተፈናቃይ መጠለያዎችን እንዲያከብሩ እንዲሁም ሲቪሎች በብዛት በተሰባሰቡባቸው አካባቢዎች ከባድ መሣሪያ ከመጠቀም እንዲቆጠቡ አሳስቧል።

አዲስ በተያዘው የፈርንጆች ዓመት ብቻ እስከ አሁን 400 የሚሆኑ ሰዎች መፈናቀላቸውንና ይህም ባለፈው ሳምንት ሪፖርት ከተረገው ቁጥር እጥፍ የጨመረ መሆኑን የኮሚሽኑ ቃል አቀባይ ማቲው ሳልትማርሽ አስታውቀዋል።

ለሃገሪቱ ሕዝብና ለቀጠናው ሲባል የተራዘመው ጦርነት መቋጫ እንዲያገኝም ጥሪ አስተላልፈዋል።

በኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ያለው ቀውስ የተረሳ መሆኑንና ለሃገሪቱ ከተጠየቀው የገንዘብ ድጋፍ ውስጥ እስከ አሁን የተገኘው 10 በመቶ ብቻ መሆኑንም ቃል አቀባዩ አስታውቀዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG