በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአፍሪካ ቀንድን የመታው ማዕበል ከሰላሣ በላይ ሰው ገደለ


የአፍሪካ ቀንድ አካባቢን ባለፉት ሁለት ቀናት የመታው እጅግ የከበደ ዝናብ ያስከተለው የሃሩር አውራጃ ማዕበልና ውሽንፍር ለሰላሣ ሰው ሞት ምክንያት ሆኗል። ቅዳሜና ዕሁድ የጣለው “ሳይክሎን ሳጋር” የሚል ስያሜ የተሰጠው የውቅያኖስ ማዕበል ኃይል በምሥራቅ አፍሪካ አካባቢዎች ላይ እስከአሁን ከተመዘገቡት ሁሉ እጅግ የበረታው እንደሆነ ባለሥልጣናቱ አስታውቀዋል።

የአፍሪካ ቀንድ አካባቢን ባለፉት ሁለት ቀናት የመታው እጅግ የከበደ ዝናብ ያስከተለው የሃሩር አውራጃ ማዕበልና ውሽንፍር ለሰላሣ ሰው ሞት ምክንያት ሆኗል።

ቅዳሜና ዕሁድ የጣለው “ሳይክሎን ሳጋር” የሚል ስያሜ የተሰጠው የውቅያኖስ ማዕበል ኃይል በምሥራቅ አፍሪካ አካባቢዎች ላይ እስከአሁን ከተመዘገቡት ሁሉ እጅግ የበረታው እንደሆነ ባለሥልጣናቱ አስታውቀዋል።

በተለይ የሶማሊያን ዋና ከተማ ሞቃዲሾን የመታው ማዕበልና የወረደው ዶፍ ዝናብ ስድስት ሰው መግደሉን፤ ከሦስት መቶ በላይ ቤቶችን ማጥለቅለቁን የከተማዪቱ ከንቲባ አብዲራህማን ኦስማን ለቪኦኤ ገልፀዋል።

በስተሰሜን ባለችው ተገንጣይዋ ሶማሊላንድ አውዳል፤ ሳህልና ሳላል አካባቢዎች ላይ ደግሞ ቢያንስ ሃያ አምስት ሰው መሞቱን ባለሥልጣናቷ የተናገሩ ሲሆን ከሰለባዎቹ አብዛኞቹ የሞቱት በደራሽ ጎርፍ ተወስደው መሆኑን የአካባቢዎቹ ነዋሪዎች አመልክተዋል።

ሌሎች ሃያ ሰባት ሰዎች የደረሱበት እስከአሁን እንደማይታወቅና 12 ሰዎች መጎዳታቸውን የሶማሊላንድ ፕሬዚዳንት ፅሕፈት ቤት አስታውቋል።

በከባዱ ዝናብ ወደ ስድስት መቶ ሰባ ሺህ የሚደርስ ሰው መጎዳቱን፣ እጅግ የሰፉ ማሳዎች ላይ ያለ ሰብል መውደሙንና ከሶማሊላንድ የእንሥሳት ሃብት ሰማንያ ከመቶ ያህል መውደሙንም የፕሬዚዳንቱ ፅሕፈት ቤት መግለጫ አስታውቆ ለግዛቲቱ ዓለምአቀፍ እርዳታ እንዲደርስ ተማፅኗል።

ጂቡቲ ውስጥ ሁለት ሰዎች በከባድ ዝናብ ምክንያት መሞታቸውን፣ ሃያ ሺህ ሰው በዶፍና በጎርፉ መጎዳቱን፣ ሶማሊላንድ ውስጥ አሥር ሺህ ሰው መፈናቀሉን፣ ፑንትላንድ ውስጥም ከደረሰው ጉዳት በተጨማሪ የመኖሪያ ቤቶችና አሣ ማስገሪያ ጀልባዎች መውደማቸውን የኖርዌይ የስደተኞች ጉዳዮች ምክር ቤት የሚባለው ግብረሰናይ ድርጅት አስታውቋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG