የአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ከምንጮቹ እንዳረጋገጠው የተቃውሞ ሰነዱ ወደ 1ሺሕ በሚጠጉ ሠራተኞች የተፈረመና ከዚህ በፊት "ታይቶ የማይታወቅ” ነው።
ባለፈው ዓመት ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ በሶሪያ የሚከተሉትን ፖሊሲ በመቃወም ወደ ሃምሳ የሚጠጉ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቶች ድምፃቸውን ማሰማታቸውን በሶሪያ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ሮበርት ፎርድ ተናግረዋል።
በኦባማ አስተዳድር የአውሮፓና የዩሬዥያ ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ላውራ ኬኔዲ በትራምፕ አስተዳድር ላይ የወጣውን የተቃውሞ ሰነድ አስመልክቶ ሲናገሩ፤ በዚህ ፖሊሲ ዙሪያ የውጭ ጉዳይ ሠራተኞች ስጋት ያካተተ ነው። በተለይ የሕጉ ዝርዝር አፈጻጸም ላይ አጠቃላይና ዝርዝር ትእዛዞች አለመካተታቸውን ዲፕሎማቶቹ አልተስማሙባቸውም።
"በዓይነቱ የተለየ ዘመን ላይ ነው ያለንው።" ብለዋል የቀድሞ ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር።
ሰነዱ “የተቃውሞ ፍኖት” በሚል የተጠራ ሲሆን፤ የትራምፕ አስተዳድር ያወጣው ፕሬዝደንታዊ ትእዛዝ “ሊያሳካ ያሰበውን ግብ የማይመታና እንዲያውም በአንጻሩ አሉታዊ የሆኑ ተጽኖዎችን የሚያሳድር ነው” ይላል።
የዩናይትድ ስቴይትስ የውጭ ጉዳይ መስሪያቤት በሰነዱ ላይ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥቧል። በተለይ ሰነዱን የፈረሙ ሰዎችን ቁጥርና በመስሪያቤቱ ያላቸውን ስልጣን አልገለጸም።
የዋይት ሃውስ ቤተመንግሥት ቃል አቀባይ ሾን ስፓይሰር፤ የፕሬዝደንት ትራምፕን የስደተኞች ትእዛዝ የሚቃወሙ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ሠራተኞች “ወይ ሥራውን ማስፈጸም፤ አሻፈረኝ ካሉ መልቀቅ ይችላሉ” ብለዋል። አያይዘውም “ይሄ የአሜሪካ ደህንነትን ይመለከታል”