የኤርትራ ዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን መሀመድ ሳለህ የኤርትራ መሬት በህገ ወጥ በኢትዮጵያ ሲያዝ፣ አይቶ እንዳላዬ ቸል በማለት የመንግስታቱን ድርጅት ከሰዋል።
ኢትዮጵያ የኤርትራን ነጻ ግዛት እንደያዘች ሲሆን፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የዚህን እርምጃ አሳሳቢነት ቸል ማለቱን መርጦአል። የኤርትራና የኢትዮጵያ ድንበር አካላይ ኮሚሽን ዉሳኔዉን ከሰጠ ስምንት ዓመታትና ኮሚሽኑ ሃላፊነቱን አጠናቆ ያካለለዉን ካርታ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ካሳወቀ በሁዋላ፣ የኢትዮጵ ከህግ ዉጭ የኤርትራን ግዛት መቆጣጠርና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጉዳዩን ቸል ማለት፣ የሁለቱ አገሮች ግጭት መቀጠል ለኤርትራና ኢትዮጵያ ህዝቦች ከባድ ሸክም ከመሆኑም በላይ የአካባቢዉን ሁኔታ የሚያወሳስብ ነዉ ብለዋል።
የኢትዮጵያ ዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ስዩም መስፍን ዛሬ በመንግስታቱ ድርጅት ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር እንደ አዉሮፓ አቆጣጠር ከ1990 ዎቹ ወዲህ ኤርትራ በርካታ ጎሬቤቶችን ወራለች፣ የመንግስታቱ ድርጅት ድረ ገጽ የኤርትራ መንግስት ያለ ምንም ትንኮሳ ኢትዮጵያን ወሮ ኢትዮጵያ ተከላክላ የኤርትራን ሰራዊት መመለስዋን ያሳያል ሲሉ በዋቢነት ጠቅሰዋል።
ምንም እንክዋን የተባባበሩት መንግስታትን ህግ ጥሳ ኢትዮጵያን ብትወርም ኤርትራ ዛሬ ኢትዮጵያ ወረረችኝ የሚል ዘመቻ ይዛለች ብለዋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ድንበሩን ለማካልል ያቀረበዉ ካርታ ላይ፤ ቁጭ ብለን እንወያይ በሚለዉ የኢትዮጵያ ጥያቄ ያልተስማማችዉም ኤርትራ ናት ብለዋል። አቶ ስዩም መስፍን
”ድንበሬ ተያዘ” የሚለዉ የኤርትራ ግምት ነዉ ያሉት አቶ ስዩም መስፍን ዉዝግብ ካለ፣ ዉዝግቡ የሚመለከታቸዉ አካላት ሃላፊነት ካልሰጡት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የማደራደር ስልጣን የለዉም ብለዋል።
ዘገባውን ያድምጡ!