በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኦሣማ መገደል እና ያለም አስተያየት


ሻንክስቪል-ፔንሲልቬንያ፤ በወደቀው አይሮፕላን የመታሰቢያ ሥፍራ ላይ "አልረሣሁትም" የሚል መልዕክት የያዘ አሜሪካዊ
ሻንክስቪል-ፔንሲልቬንያ፤ በወደቀው አይሮፕላን የመታሰቢያ ሥፍራ ላይ "አልረሣሁትም" የሚል መልዕክት የያዘ አሜሪካዊ

የኦሣማ ቢን ላደን መገደል ወሬ በጥቅሉ በመላው መካከለኛው ምሥራቅ እንደመልካም ዜና ቢወሰድም የአልቃይዳ መረብ እንዲህ በቀላሉ ይበጣጠሳል ተብሎ ግን እንደማይታመን እየተነገረ ነው፡፡

የኦሣማ ቢን ላደን በዩናይትድ ስቴትስ ዘመቻ ፓኪስታን ውስጥ መገደሉ ሃገሪቱ "ለሽብርተኞች ከለላ እንደምትሰጥ ይመሠክራል" ሲሉ የሕንድ ባለሥልጣናት አለን የሚሉትን "ብርቱ ሥጋት" ተናግረዋል፡፡ ከሁለት ዓመት በፊት የደረሰውን የሙምባዩን የሽብር ጥቃት ያቀናበሩትን ለፍርድ እንድታቀርባቸው ለፓኪስታን ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የኦሣማ ቢን ላደን መገደል በአብዛኛው የዓለም ክፍል ደስታን እንዳጫረ በስፋት እየተነገረ ቢሆንም በተገደለባት ፓኪስታን ውስጥ ግን ብዙም ወሬ የለም፤ "ዝም፣ ዝም" ሆኗል እየተባለ ነው፡፡

በዓለም ግዙፉ የእሥልምና ምዕመናን ቁጥር ባለባት ኢንዶኔዥያ ስለቢን ላደን መገደል የተሰማ ኀዘን የለም፤ እንዲያውም እጅግ የበረከተ ቁጥር ያለው ሕዝብ ለዩናይትድ ስቴትስ ድጋፉን እየገለፀ መሆኑ ተነግሯል፡፡ ይሁን እንጂ ፅንፈኛና አክራሪ የሚባሉ ቡድኖች ለበቀል ሊነሣሱ እንደሚችሉ ደግሞ የሚጠቋቁሙ ሥጋቶች አሉ፡፡

የአሜሪካ ድምፅ ሪፖርተሮች ከካይሮ፣ ከኒው ደልሂ፣ ከኢስላማባድ እና ከጃካርታ ያስተላለፏቸው ዘገባዎች አሉ፤ ሰሎሞን አባተ ጨምቆ ለመፅሔት አዘጋጅቷቸዋል፡፡

ዝርዝር ዘገባውን ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG