የዩናይትድ ስቴይትስ ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ የአልቃይዳ መሪ የሆነውና በአለም አንደኛ ተፈላጊ አሸባሪ የሆነው ኦሳማ ቢንላድን እሁድ መገደሉን አስታወቁ።
በዩናትድ ስቴይትስ ልዩ ሃይሎች የ53 ዓመቱ ኦሳማ መገደሉን ለአሜሪካ ህዝብ ፕሬዝደንት ኦባማ ከተናገሩ በኋላ አሜሪካኖች በዋይት ሃውስ ቤተመንግስትና በተለያዩ አካባቢዎች ባንዲራ በመያዝ፣ የመኪና ጡሩምባ በመንፋት ደስታቸውን ገልጸዋል።
በመስከረም አንዱ ጥቃት የዩናይትድ ስቴይትስ ላይ እንዲያነጣጥር ያስተባበረ ነው በሚል የሚፈለገው ኦሳማ በምስራቅ አፍሪካም በኬንያና ታንዛኒያ የሚገኙ የዩናትድ ስቴይትስ ኢምባሲዎች የደረሱ ፍንዳታዎችን አልቃይዳ ማቀናበሩንና ማስፈጸሙን የምርመራ ውጤቶች አስታውቀዋል።
ከዚያን ጊዜ ጀመሮ ኦሳማ ቢንላድን ተሸሽጎ የሚኖርበት አይታወቅም ነበር።