በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“እኔን ፍለጋ የመጣው ወንድሜ ተገደለ” - የ16 ዓመት ሟች ወንድም


በኦሮሚያ የተለያዩ ከተሞች የተቃውሞ እንቅስቃሴ መቀጠሉንና የሰው ሕይወት መጥፋቱን ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች ገለፁ።

በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ከተሞች ተቃውሞዎች መቀጠላቸውን ተቃውሞዎቹ በተደረገባቸው አካባቢዎች ያሉ አንዳንድ ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምጽ ገለጹ። በሙከጡሪ ከተማ ትንናት አንድ የ16 ዓመት ወጣት መገደሉን ወድንሙ ገልፆልናል። በሰሜን ሸዋ ዞን ደገም ወረዳ ነዋሪ የሆነ ሌላ ምንጭ ደግሞ “በሰላማዊ መንገድ ይካሄድ በነበረ ሰልፍ ላይ ተኩስ ተከፍቶበናል” ብሎናል።

በሌላ በኩል በጅማ ዩኒቨርስቲ የኢንጅነሪንግ እና የኮምፒዩተር ሳይንስ ተማሪዎች ከጅግጅጋ ዩኒቨርስቲ የወጡ ከ4,000 በላይ ተማሪዎችና መምሕራን የሚማሩበት ዩኒቨርስቲ ሊመደቡ ይገባል የሚል ጥያቄን ይዘው መውጣታቸውን ተናግረዋል።

ከኦሮሚያ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች መረጃ ለማግኘት ሞክረን ስልካቸው ስለማይነሳ ማግኘት ሳንችል ቀርተናል።

“እኔን ፍለጋ የመጣው ወንድሜ ተገደለ” - በሙከጡሪ ከተማ የ16 ዓመት ሟች ወንድም
please wait

No media source currently available

0:00 0:11:19 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG