ዋሽንግተን ዲሲ —
በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ከተሞች ካለፈው ሣምንት ዕረቡ ነሐሴ 17 ቀን ጀመሮ ለአምስት ቀናት ተጠርቶ የነበረው እቤት የመቀመጥ አድማ የተያዘለትን ግብ በመምታቱ በሦስተኛው ቀን እንዲቋረጥ መደረጉን
አስተባባሪዎቹ በማኅበራዊ ሚዲያ ከገለጹ በኋላ በአንዳንድ ከተሞች ከቅዳሜ ጀምሮ የትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት የተንቀሳቀሱ አሽከርካሪዎች ሥራ ላቋረጡበት ቅጣት እንዲከፍሉ መባላቸውና አንዳንዶቹም ሱቆቻቸው እንደታሸጉባቸው ገለፁ። የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ማንም ዴሞክራሲያዊ መብቱን ተጠቅሞ ተቃውሞውን በአድማ ቢገልጽ መብቱ መሆኑን መናገራቸው ይታወሳል።
በተያያዘም በቢሾፍቱ ሆራ አርሰዲ ሃይቅ ሕይወታቸው ለጠፋ ሰዎች በክልሉ መንግስት የተሰራው ኃውልት ተቃውሞ ገጥሞታል።
ቀጣዩ የጽዮን ግርማ ዘገባ ሁሉንም ይዳስሳል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ