ዋሺንግተን ዲ.ሲ. - አዲስ አበባ —
የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ - ኦፌኮ ባለፈው ዕሁድ አዲስ አበባ ላይ በጠራው ህዝባዊ ስብስባ ኦሮሚያ ውስጥ የሚገኙ ከተሞችን ከአዲስ አበባ አስተዳደር ጋር ለማስተሳሰር በወጣው ማስተር ፕላን ላይ ተቃውሞውን ገልጿል፡፡
ኦፌኮ ይህንን ያሳወቀው ያካሄደውን ምክክር ተከትሎ ባወጣው የአቋም መግለጫ የከተሞቹን ነዋሪዎች የሚጎዳ ነው የሚል ድምዳሜ ላይ በመድረሱ መሆኑ ታውቋል፡፡
“የኦሮሞ ገበሬዎች እየተነቀሉ ቦታቸው በሊዝ የሚሰጠው ለመሬት ቅርምት እንጂ ለልማት አይደለም” በማለት ኦፌኮ ተቃውሞውን አሰምቷል።
ዋና ፀሐፊው አቶ በቀለ ነጋ ለቪኦኤ የሰጡትን መግለጫ የያዘውን የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡