በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአትላንታው የኦሮሞ ተወላጆች ጉባዔ


ፕሮፌሰር ሕዝቅዔል ገቢሣ
ፕሮፌሰር ሕዝቅዔል ገቢሣ

ከተለያዩ የሕይወት መስኮች የተሰባሰቡ ከስድስት መቶ በላይ የሚሆኑ የኦሮሞ ተወላጆች በጆርጂያ ግዛት ዋና ከተማ አትላንታ ላይ ያደረጉት ጉባዔ ተጠናቅቆ የሥራ ሠነድ አውጥቷል፡፡

የጉባዔው ዓላማ የተለያዩ ሃሣቦችና አቋሞች ያሏቸው የኦሮሞ ድርጅቶች ኃላፊነት ባለው መንገድ እንዲንቀሣቀሱና በአንድ መድረክ እንዲታገሉ ለማስቻል፣ በኦሮሞ ሕዝብ ዘንድ የነቃና ሥፋት ያለው ውይይት ለማካሄድ መሆኑን ከአስተባባሪዎቹ አንዱ የሆኑት ፕሮፌሰር ሕዝቅዔል ገቢሣ ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡

የሠብዓዊ ድጋፍ ሰጭ ድርጅት እንዲቋቋምም ሃሣብ ቀርቧል፡፡

“የኦሮሞ አብዮት” ሲል የጉባዔው መግለጫ በጠራው እንቅስቃሴ ውስጥ ከሌሎች ነፃነት አፍቃሪ ሕዝቦች ጋርም እጅ ለእጅ ለመያያዝ እንደሚሠሩ ተሣታፊዎቹ አመልክተዋል፡፡

ከፕሮፌሰር ሕዝቅዔል ገቢሣ ጋር ያደረግነውን ሙሉ ቃለ-ምልልስ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

የአትላንታው የኦሮሞ ተወላጆች ጉባዔ
please wait

No media source currently available

0:00 0:17:11 0:00

XS
SM
MD
LG