አዲስ አበባ —
በኦሮሚያ ክልል የተደረገውን ይቅርታ “ገንቢ” ሲሉ የገለፁት የመድረክ ሊቀ መንበር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ በሀገሪቱ ያለውን ሁኔታ ለማረጋጋት ግን የፖለቲካ መሪዎቻችን አባሎቻችንና በፖለቲካ አመለካከታቸው ብቻ የታሰሩ ሌሎችም መፈታት አለባቸው ብለዋል።
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ቃል አቀባይ አቶ አዲሱ አረጋ በበኩላቸው በፖለቲካ አመለካከቱ ምክንያት የታሰረ ሰው የለም ብለዋል። የተደረገው ይቅርታም የክልሉ ፕሬዚዳንት በመደበኛነት የሚያደርጉት እንጂ ከምንም ወቅታዊ ሁኔታ ጋር የተገናኘ አይደለም ብለዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ።