በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኦሮሚያ ክልል የአንዳንድ አካባቢዎች የጸጥታ ችግር “የወባ ወረርሽኝን እያባባሰ ነው”


በኦሮሚያ ክልል የአንዳንድ አካባቢዎች የጸጥታ ችግር “የወባ ወረርሽኝን እያባባሰ ነው”
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:38 0:00

በኦሮሚያ ክልል የአንዳንድ አካባቢዎች የጸጥታ ችግር “የወባ ወረርሽኝን እያባባሰ ነው”

በኦሮሚያ ክልል በአንዳንድ አካባቢዎች ያለው የጸጥታ ችግር፣ የወባ ትንኝን ለመቆጣጠር እና የበሽታውን ስርጭት ለመግታት ለሚከናወነው ተግባር ዕንቅፋት እንደፈጠረበት፣ የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ።

በክልሉ ጤና ቢሮ የወባ በሽታ ማስወገድ ቡድን መሪ አቶ ጃዋር ቃሲም፣ የወባ በሽታን ለመከላከል እና ለማከም የሚረዱ ግብአቶች እጥረት መኖሩን ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸው፣ የሰላም ዕጦቱ ደግሞ ይበልጥ እንዳባባሰው አመልክተዋል።

በኢሊአባቦር ዞን፣ ከሁለት ሳምንት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ቢያንስ ሰባት ሰዎች በወባ በሽታ እንደሞቱ፣ የዞኑ ጤና ጽሕፈት ቤት ሓላፊ አቶ አብዮት ታምሩ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

የተባበሩት መንግሥት የሰብአዊ ርዳታ ማስተባበርያ ቢሮ(UN-OCHA) ሰሞኑን ባወጣው ሪፖርት፣ የወባ በሽታ ከተስፋፋባቸው የአገሪቱ አካባቢዎች ውስጥ 50 በመቶዎቹ በኦሮሚያ ክልል እንደሚገኙ ገልጿል፡፡

የኦሮሚያ ክልል ምዕራባዊ ዞኖች፣ የዐማራ እና የደቡብ ምዕራብ ክልሎች እንደቅደም ተከተላቸው፣ ከፍተኛ የበሽታው ተጠቂዎች እንደሚገኙባቸው፣ ሪፖርቱ አክሎ አመልክቷል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG