በኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ታጣቂዎችና በመንግስት የጸጥታ አስከባሪ ኃይሎች መካከል ግጭት በቀጠለባቸዉ የኦሮሚያ ክልል ዞኖች የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት ተቋርጦ መቀጠሉን ነዋሪዎች ተናገሩ።
የስልክ አገልግሎቱ በተለይ በጉጂ፣ በቄለም ወለጋ፣ በሆሮ ጉዱሩና ሰሜን ሸዋ ዞኖች መቋረጡን የገለጹት ነዋሪዎቹ፣ ይህም በተለይም በተማሪዎች ላይ ጫና እየፈጠረ መሆኑን አክለዉ ተናግረዋል።
የአሜሪካ ድምፅ ከኢትዮ ቴሌኮም ምላሽ ለማግኘት ያደረገዉ ተደጋጋሚ ጥረት አልተሳካም።
መድረክ / ፎረም