በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ግጭት ባለባቸው አንዳንዶቹ የኦሮሚያ ዞኖች የስልክ አገልግሎት መቋረጡን ነዋሪዎች ተናገሩ


የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ
ግጭት ባለባቸው አንዳንዶቹ የኦሮሚያ ዞኖች የስልክ አገልግሎት መቋረጡን ነዋሪዎች ተናገሩ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:25 0:00

በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን እንደዚሁም ምዕራብ ወለጋ እና ቄለም ወለጋ ዞኖች፣ የስልክ አገልግሎት ረዘም ላለ ጊዜ መቋረጡን የገለጹ የአካባቢው ነዋሪዎች፣ በኢኮኖሚያዊና በማህበራዊ እንቅስቃሴዎች ከፍተኛ ተጽእኖ እያደረሰ መሆኑን ተናገሩ።

የአገልግሎቱ መቋረጥ ከአካባቢው የጸጥታ ችግር ጋራ ተዳምሮ፣ አሳሳቢ እንደሆነባቸውም አመልክተዋል።

በምዕራብ ወለጋ እና ቄለም ወለጋ ዞኖች በሚገኙ በርካታ ወረዳዎች ፣ በተለይ የኢንተርኔት አግልግሎት ከተቋረጠ ከአራት ዓመታት በላይ ማስቆጠሩን ነዋሪዎች ጠቅሰዋል።

በሰሜን ሸዋ ዞን የሚገኙ ነዋሪዎች ደግሞ ከሁለት ሳምንት በላይ ለሆነ ጊዜ የስልክ ግንኙነት ተቋርጧል ብለዋል።

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ በግጭት አካባቢዎች እንደዚህ አይነት ችግሮች እንዳሉ አምነ፣ በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥበዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG