በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኦነግ በኦሮሚያ ክልል በወር ውስጥ እንደተገደሉ ለገለጻቸው 150 ሰዎች መንግሥትን ተጠያቂ አደረገ

ኦነግ በኦሮሚያ ክልል በወር ውስጥ እንደተገደሉ ለገለጻቸው 150 ሰዎች መንግሥትን ተጠያቂ አደረገ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:45 0:00

ኦነግ በኦሮሚያ ክልል በወር ውስጥ እንደተገደሉ ለገለጻቸው 150 ሰዎች መንግሥትን ተጠያቂ አደረገ

ተቃዋሚው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር(ኦነግ)፣ በኦሮሚያ ክልል፣ ባለፈው አንድ ወር ጊዜ ውስጥ፣ ከ150 በላይ ንጹሐን ዜጎች፣ በአውሮፕላንና በከባድ መሣሪያዎች ጥቃት እንደተገደሉ፣ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

ግንባሩ፣ ከትላንት በስቲያ ባወጣው መግለጫ፣ ለኹሉም የሰላማውያን ዜጎች ግድያዎች የመንግሥት ኀይሎችን ተጠያቂ አድርጓል።

መንግሥት “ኦነግ ሸኔ” በሚለው ታጣቂ እና መሰል ኀይሎች ላይ ርምጃ እየወሰደ እንደኾነ የገለጹት፣ የክልላዊ መንግሥቱ የኮምዩኒኬሽን ቢሮ ሓላፊ አቶ ኀይሉ አዱኛ ግን፣ ወታደራዊ ርምጃው በሰላማውያን ዜጎች ላይ ያነጣጠረ ነው፤ መባሉን አስተባብለዋል። የኦነግ መግለጫም፣ “በሁለቱ ቡድኖች መካከል ያለውን ትብብር የሚያሳይ ነው፤” ሲሉ ውንጀላውን አጣጥለዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG