በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጠቅላይ ሚኒስትሩ በዓለ ሢመት የታዩት ተፃራሪ ትዕይንቶች እንዳሳሰባቸው ተቃዋሚዎች ተናገሩ


ፎቶ፦ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና/ኤኤፍፒ/ ዶ/ር ራሄል ባፌ/ቪኦኤ/
ፎቶ፦ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና/ኤኤፍፒ/ ዶ/ር ራሄል ባፌ/ቪኦኤ/

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን አምስተኛ ዓመት በዓለ ሢመት በማስመልከት፣ በኦሮሚያ ክልል በርካታ አካባቢዎች የድጋፍ፣ በአማራ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች ደግሞ የተቃውሞ ሰልፍ ተካሒዷል።

ከኹለቱም ክልሎች፣ በሰልፉ የተሳተፉ አስተያየት ሰጪዎች፣ ለሰልፍ ስለወጡበት ምክንያት ተናግረዋል፡፡

በድጋፍ እና በተቃውሞ ስለተደረጉት የሰልፍ ትዕይንቶች፣ አስተያየታቸውን የሰጡን የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ሊቀ መንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና፣ “በኹለቱ ክልሎች የተካሔዱት ሰልፎች በለውጡ ሒደት፣ የወደፊት አቅጣጫ እና በልዩ ልዩ በርካታ ጉዳዮች ላይ፣ ዛሬም ድረስ ስምምነት ላይ አለመደረሱን እንደሚያሳይ አስረድተዋል፡፡

“በድርድር ላይ የተመሠረተ የፖለቲካ መረጋጋት ካልተፈጠረ፣ ችግሮች ተባብሰው አስከፊ ደረጃ ላይ ሊደርሱ ይችላሉ፤” ሲሉም አሳስበዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ ምክትል ሊቀ መንበር እና የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ዋና ጸሐፊ ራሄል ባፌ/ዶር./ በበኩላቸው፣ “ሰልፉ በተለያየ ጽንፍ ላይ በሚገኙ ልሂቃንና በመንግሥት አካላት መሪነት የሚካሔድ ነው። ይህም ካለፈው ስሕተት ባለመማር፣ አገሪቱን ለሌላ ዙር ችግር ሊዳርግ የሚችል አካሔድ ነው፤ በመኾኑም አፋጣኝ መፍትሔ ያሻዋል፤” በማለት አስገንዝበዋል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

በጠቅላይ ሚኒስትሩ በዓለ ሢመት የታዩት ተፃራሪ ትዕይንቶች እንዳሳሰባቸው ተቃዋሚዎች ተናገሩ
please wait

No media source currently available

0:00 0:11:24 0:00

XS
SM
MD
LG