በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከቁሉቢ ሲመለሱ ታግተው የቆዩ 11 ሰዎች ተለቀቁ


ታኅሳስ 19 ከቁሉቢ ገብርኤል ንግሥ በዓል በመመለስ ላይ ሳሉ ከአንድ መኪና ውስጥ ታግተው የተወሰዱ 11 ሰዎች መለቀቃቸውን ከታጋቾቹ አንዱ እና ቤተሰቦቻቸው ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ፡፡

በመኪናው ተሳፍረው ከነበሩት ሰዎች ውስጥ፣ “በአዲስ አበባ ከተማ አቃቂ አካባቢ ነዋሪ የነበሩ አምስት የአንድ ሰፈር ሰዎች ተገድለው ከነመኪናው ተቃጥለዋል” ታግቶ የተለቀቀው ገልጿል፡፡

ከቁሉቢ ሲመለሱ ታግተው የቆዩ 11 ሰዎች ተለቀቁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:18 0:00

እርሱን ጨምሮ ታግተው የተወሰዱት ደግሞ “የማስለቀቂያ ገንዘብ ክፈሉ” በሚል ከፍተኛ ድብደባ እንደተፈጸመባቸውም ተናግሯል፡፡

ከታጋች ቤተሰቦች መካከል የሆኑ አንድ አባት ደግሞ፣ ተለቅቀው የመጡት ታጋቾች የአካል እና የስነልቦና ጉዳት እንደደረሰባቸው አመልክተዋል፡፡

ስለ ጉዳዩ ከመንግሥት ወገን አስተያየት ለማግኘት ያደረግነው ተደጋጋሚ ጥረት አልተሳካም፡፡

የዚህን ዘገባ ዝርዝር ከተያያዘው ፋይል ያድምጡ፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG