በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"በመዳወላቡ ወተት በመሸጥ ላይ የነበሩ ሁለት እናቶች በጥይት ተገድለዋል"- ነዋሪ


በባሌ ዞን በመዳ ወላቡ ወረዳ "መዳ" በተባለች ቀበሌ የገበያ ቦታ ላይ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ በተፈጠረ ግጭት የሦስት ሰዎች ሕይወት ማለፉንና ሰባት ሰዎች መቁሰላቸውን ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል። ከሟቾቹ ውስጥም አንዲት የስምንት ልጆች እና አንዲት የሰባት ልጆች እናት ወተት በመሸጥ ላይ እያሉ በመከላከያ በተተኮሰ ጥይት መገደላቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል።

በኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞን በመዳዋላቡ ወረዳ በዛሬው ዕለት በገበያ ቦታ ላይ በመከላከያ በተተኮሰ ጥይት ሦስት ሰው ሞቶ ሰባት ሰዎች መቁሰላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎችና ስሙን መግለፅ ያልፈለገ የወረዳው ባለሥልጣን አስታወቀ።

በሌላ በኩል በሐረሪ ክልል ስር በሚገኘው ሐማሬሳ መጠለያ ጣቢያ ተጠልለው በሚገኙ የሶማሌ ክልል ተፈናቃዮችና በፀጥታ አካላት መካከል በተፈጠረ ግጭት አራት ግለሰቦ መሞታቸውና 11 ሰዎች መቁሰላቸውን የምስራቅ ሐረርጌ ዞን አስተዳዳሪ አስታውቀዋል።

በተጨማሪም ከዛሬ ጀምሮ እስከ ረቡዕ ድረስ የሚቆየው የንግድ እንቅስቃሴ ማቆም አድማ በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል ከተሞች ተግባራዊ መደረግ መጀመሩን ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ገልፀዋል።

የሁሉንም ዘገባዎች ዝርዝር ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

"በመዳወላቡ ወተት በመሸጥ ላይ የነበሩ ሁለት እናቶች በጥይት ተገድለዋል"- ነዋሪ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:29 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG