በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኦሮሚያ ክልል ያለው የሲቪሎች ግድያና እገታ መፍትሔ እንዲሰጠው ተጠየቀ


በኦሮሚያ ክልል ያለው የሲቪሎች ግድያና እገታ መፍትሔ እንዲሰጠው ተጠየቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:25 0:00

በኦሮሚያ ክልል ያለው የሲቪሎች ግድያና እገታ መፍትሔ እንዲሰጠው ተጠየቀ

መንግሥት በኦሮሚያ ክልል እየተባባሰ ለኼደው የሰላማዊ ሰዎች ግድያና እገታ ዕልባት ሊያመጣ የሚችል እርምጃ እንዲወስድ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጥሪ አቅርበዋል።

ለግድያውና ለእገታው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊትን ተጠያቂ ያደረገው ኢዜማ፣ መንግሥት ድርጊቱን በወታደራዊ ዘመቻ እንዲከላከል ጠይቋል፡፡

የፓርቲው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ዶ/ር ሙሉዓለም ተገኝወርቅ መንግሥትን በቸልተኝነት ወቅሰዋል፡፡

የኦፌኮ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና በበኩላቸው፣ በግድያና በእገታ ተግባሩ የተለያዩ አካላት እንደሚሳተፉ ገልጸው፣ ገለልተኛ ምርመራ እንዲደረግ ጠይቀዋል፡፡

ችግሩ ሊፈታ የሚችለው ሁሉን አቀፍ በሆነ ፖለቲካዊ ድርድር ነው ሲሉም ፕሮፌሰሩ ተናግረዋል፡፡

በዩናይትድ ስቴትስ የሚገኙት የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ቃል አቀባይ አቶ ኦዳ ታርቢ ሰሞኑን ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ምላሽ፣ ከሰላማዊ ሰዎች ግድያና እገታ ጋር በተያያዘ በድርጅታቸው ላይ የሚቀርበውን ውንጀላ አጣጥለዋል፡፡

በጉዳዩ ላይ ከፌዴራል መንግሥት ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም፡፡

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG