በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ግጭቶች ቢቀጥሉም በታንዛኒያው ድርድር ተስፋ እንዳላቸው የክልሉ ነዋሪዎች ተናገሩ


ግጭቶች ቢቀጥሉም በታንዛኒያው ድርድር ተስፋ እንዳላቸው የክልሉ ነዋሪዎች ተናገሩ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:55 0:00

ግጭቶች ቢቀጥሉም በታንዛኒያው ድርድር ተስፋ እንዳላቸው የክልሉ ነዋሪዎች ተናገሩ

በፌዴራል መንግሥት እና በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት መካከል የተጀመረው ሁለተኛ ዙር የሰላም ድርድር፣ በታንዛንያ - ዳሬ ሰላም እየተካሔደ ባለበት በዚኽ ሰሞን፣ በኦሮሚያ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች ግጭቶች እንደቀጠሉ ነዋሪዎች ተናገሩ።

ከሰሜን ሸዋ ዞን ያያ ጉሌሌ ወረዳ እና ከምሥራቅ ቦረና ዞን ጎሮ ዶላ ወረዳ፣ ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየታቸውን የሰጡ ነዋሪዎች እንደገለጹት፣ በአካባቢያቸው ግጭቶች እንደቀጠሉ ቢኾኑም፣ ድርድሩ ውጤት እንደሚያመጣ ተስፋ ያደርጋሉ።

ከድርድሩ ጋራ በትይዩ የቀጠሉትን ግጭቶች አስመልክቶ፣ ከክልሉ የጸጥታ እና አስተዳደር ቢሮ፣ እንዲሁም ከፌዴራሉ መንግሥት የኮምዩኒኬሽንስ አገልግሎት ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም።

በተያያዘ ዜና፣ የፌዴራል መንግሥቱ ከታጣቂው ኀይል ጋራ እያካሔደ ያለውን ድርድር ይዘት እና ዝርዝር ኹኔታዎች ለሕዝብ ግልጽ እንዲያደርግ፣ አምስት ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ ባወጡት መግለጫ ጠይቀዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG