በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጨፌ ኦሮምያ መደበኛ ጉባዔ እና የክልሉ የፀጥታ ችግር


የጨፌ ኦሮምያ መደበኛ ጉባዔ እና የክልሉ የፀጥታ ችግር
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:30 0:00

የጨፌ ኦሮምያ መደበኛ ጉባዔ እና የክልሉ የፀጥታ ችግር

መንግሥት በኦሮምያ ክልል ውስጥ እየታየ ያለውን የፀጥታ ችግር ለመፍታት አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወስድ የኦሮምያ ክልል ምክር ቤት አባላት ጠየቁ።

“ጨፌ ኦሮምያ” በሚል የሚታወቀው የክልሉ ምክር ቤት በማካሄድ ላይ የሚገኘው ስድስተኛ የሥራ ዘመን ስብሰባው ላይ አቤቱታ ያቀረቡት የምክር ቤቱ አባላት በታጣቂዎች ምክኒያት የሰዎች ሕይወት እየጠፋ መሆኑን ተናግረዋል።

ትናንት በጀመረው የክልሉ ሕግ አውጪዎች ስብሰባ ላይ፤ በተለይ በክልሉ እየታየ ያለው የፀጥታ ችግር ከሕይወት መጥፋት በተጨማሪ፣ ለአገልግሎቶች መቋረጥ መንስኤ እንደሆነ ተናግረዋል።

አንድ የቄለም ወለጋ ተወካይ የምክር ቤቱ አባል፤ በዞኑ ከ100 በላይ የመንግሥት ሠራተኞች በፀጥታ ችግር ምክኒያት ሕይወታቸው ማለፉን ተናግረዋል።

ከምዕራብ ወለጋ የመጡ ተወካይ ደግሞ ከአንድ ሺህ በላይ ሰዎች መገደላቸውን አስረድተዋል። እነዚህ ሰዎች የተገደሉት በምን ያህል ጊዜ ውስጥ እንደሆነ ግን አላብራሩም። የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ለምክር ቤት አባላቱ በሰጡት ምላሽ፤ “ክልሉን ሰላም እየነሱ ያሉት የኦሮሞ ሕዝብ በእጁ ያገኘውን ድል ለመንጠቅ እየጣሩ ያሉ ኃይሎች ናቸው” ብለዋል።

ችግሩን ለመፍታት የክልሉን የፀጥታ ኃይል ማጠናከር እና ሌሎች እርምጃዎችን በመወሰድ ላይ መሆኑን ገልፀው፤ ታጣቂዎች በሀገር ሽማግሌዎች አማካይነት በሰላም እንዲገቡ አሳስበዋል።

/ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ያዳምጡ/

XS
SM
MD
LG