ነቀምት —
ለኦሮምያ ችግሮች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ በኦሮምያ የተለያዩ ቦታዎች የሚስተዋሉ አለመረጋጋቶች እንዲፈቱ የኦሮምያ ክልል መንግሥትን መጠየቁን አስታወቀ።
በስድስት ነጥቦች የዘረዘራቸውን በክልሉ መፈታት አለባቸው ያላቸውን ችግሮች በግልባጭ ለጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤትና ሌሎችም ይመለከታቻዋል ላሏቸው አካላት መላካቸውን የኦሮምያ አባ ገዳዎች ህብረት ሰብሳቢ ጎበነ ሆላ ተናግረዋል።
የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻ ያለመረጋጋት ችግሩ ይፈታ ዘንድ መንግሥት ከመፍትሄ አፈላላጊው ኮሚቴ ጋር ውይይት ማድረጉን ገልፀዋል።
መንግስት ጥያቄ ካለው ቡድን ጋር ለመወያየት ዝግጁ መሆኑን ቢገልፅም ከሸማቂዎቹ እስከ አሁን ምላሽ አለመገኘቱን ነው ኃላፊው የተናገሩት።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ