በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሰሞኑ የኦሮሚያ ተቃውሞ መነሻና የተከተሉት ቀናት


ኦሮሚያ ክልል የሚካሄደው ተቃውሞ ሁለተኛ ወሩን ያዘ።

please wait

No media source currently available

0:00 0:05:16 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

ኦሮሚያ ክልል የሚካሄደው ተቃውሞ ሁለተኛ ወሩን ያዘ።

የኦሮሞ ሕዝብ የዋና ከተማይቱን የአዲስ አበባን ወደ አካባቢዋ አዋሳኝ የክልሉ ግዛቶች መስፋፋት የሚቃወም ሲሆን ሌሎች ጥያቄዎችም አሉት።

ከእነዚህም አንዱ መንግሥት ሥልጣን ከልክሎናል የሚል እንደሆነ ጠቅሳ የቪኦኤዋ ማርተ ፋን ደር ቮልፍ ተቃውሞው በኅዳር መግቢያ ከተጀመረባት ጊንጪ ከተማ ዘግባለች።

በጊንጪ ትምህርት ቤቶች ዝግ ናቸው፤ የንግድ ቤቶች ለሣምንታት ከተዘጉ በኋላ እየተከፈቱ ነው፡፡ ሆኖም ከአዲስ አበባ 80 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ትንሿ ከተማ ውጥረት ሰፍኖ ሰንብቷል።

ፖሊሶች በዋናው ጎዳና ላይ ይዘዋወራሉ፤ ጋዜጠኛን የሚያነጋግሩ ሰዎች ማንነታቸው እንዳይገለፅ ይጠይቃሉ፤

አንዲት ለሁከቱ የዐይን እማኝ የነበረች የሻይ ቤት ሠራተኛ ንግድ ቤቱ ቢከፈትም በጊንጪ ግን አሁንም ውጥረት እንዳለ ተናግራለች፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG