በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"በአሳሳ ባልና ሚስቱ ቤታቸው ውስጥ እንዳሉ ነው የተገደሉት"- ቤተሰብ


በኦሮምያ ክልል በአንዳንድ አካባቢዎች ምንም ዓይነት የተቃውሞ እንቅስቃሴ ሳይኖር ሰላማዊ ዜጎች በፀጥታ ኃይሎች መገደላቸውን የሟቾች ቤተሰቦች ለአሜሪካ ድምፅ ገለፁ።

በተለይ አሳሳ በተባለው ከተማ በመኖርያ ቤታቸው ውስጥ እንዳሉና ከመስጂድ ሲወጡ የተገደሉ ሰዎች መኖራቸውን ቤተሰቦቻቸው ተናግረዋል። በሌሎች አካባቢዎችም በተመሳሳይ ሕፃናትና አዛውንት መገደላቸውን ነዋሪዎች ገለጸዋል።

የኦሮምያ የፀጥታ አስተዳደር ቢሮ በበኩሉ ሕገ ወጥ የሆነ እንቅስቃሴን ለማስቆም በመንግሥት በኩል እርምጃ መወሰዱን ገልፆ አንዳንዶቹ ድርጊቶች ተጨማሪ ማጣራት ይፈልጋሉ ብሏል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

"በአሳሳ ባልና ሚስቱ ቤታቸው ውስጥ እንዳሉ ነው የተገደሉት"- ቤተሰብ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:11 0:00


XS
SM
MD
LG