በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሻሸመኔና ጨለንቆ ላይ ሕይወት መጥፋቱ ተገለፀ


የአሜሪካ ኤምባሲ ዜጎቹ ወደ ሻሸመኔ ከመጓዝ እንዲቆጠቡ መከረ።

ዛሬ በኦሮሚያ ክልል በተካሄዱ የተቃውሞ ሰልፎች የአምስት ሰው ሕይወት ማለፉ ተነግሯል።

አራቱ የተገደሉት ሻሸመኔ ከተማ ውስጥ በተካሄደ ሰላማዊ ሰልፍ እንደነበረና አንድ ሰው ደግሞ ምሥራቅ ሀረርጌ፣ ጨለንቆ ውስጥ መገደሉን የዐይን እማኞች ነን ያሉ ሰዎች ለቪኦኤ አገልጠዋል።

ሻሸመኔ ላይ በተካሄዱ ሰልፎች ከሰላሣ በላይ ሰው በጥይት መቁሰሉንም እማኞች ገልፀውልናል።

በሌላ በኩል ደግሞ በአምቦ ከተማና በቦኬ የተደረጉት ሰልፎች ያለ ምንም ግጭት መጠናቀቃቸውንም እማኞች ተናግረዋል።

የዛሬዎቹን የኦሮምያ ከተሞች ሰልፎች ያስተባበረ ወይም የጠራ እገሌ ነው የሚባል ወገን አለመጠቀሱና ሰዉ በየአካባቢው የወጣው በራሱ ተነሣሽነት መሆኑን ያነጋገርናቸው እማኞች አመልክተዋል።

በሰልፎቹ ላይ የተሰሙት ተመሣሣይ ጥያቄዎች በኦሮምያና በሶማሌ የድንበር አካባቢዎች በኦሮሞዎች ላይ እየተፈፀመ ያለው ጥቃትና ከሶማሌ ክልል አካባቢዎችም የሚደርስባቸው መፈናቀል ይቁሙ የሚል እንደነበረ ታውቋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ አዲስ አበባ ያለው የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ሻሸመኔ አካባቢ የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች መካሄዳቸውንና መንገዶችም እንደተዘጉ አስታውቋል።

የኤምባሲው መግለጫ በተቃውሞዎቹ ወቅት በተፈጠሩት ግጭቶች የሞቱ ሰዎች መኖራቸውንም ጠቁሟል።

የአሜሪካ ዜጎች ወደ ሻሸመኔ ከመሄድ እንዲቆጠቡ እንደ ሁልጊዜውና እንዳስፈላጊነቱም ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ኤምባሲው መክሯል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ሻሸመኔና ጨለንቆ ላይ ሕይወት መጥፋቱ ተገለፀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:17 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG