በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ሻምቡ ከተማ በተነሳ ተቃውሞ አንድ ሰው ሞቶ አራት ሰው ቆሰለ


በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ሻምቡ ከተማ ውስጥ ዛሬ ጠዋት በተነሳ ግጭት በተኩስ የአንድ ሰው ሕይወት ሲያልፍ አራት ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ።

የግጭቱ መነሻ “የአካባቢው ሰው ያላገኘው ስኳር በሕገወጥ መንገድ በሦስት ተሽከርካሪ ተጭኖ በአካባቢው ሊያልፍ አገባም” ባሉ ነዋሪዎች የተጀመረ ተቃውሞ ነው ብለውናል።

ተቃውሞውን ለመበተን በተተኮሰ ጥይት ሕይወቱ ያለፈውም በጫማ ጠረጋ ሥራ ላይ የተሰማራ የ15 ዓመት ልጅ እንደሆነ ገልፀውልናል።

በሌላ በኩል ሌሎች የኦሮሚያ ክልል ከተሞች ማለትም በምስራቅ ወለጋ ኑኑ ቁምባ ወረዳ፣ በምስራቅ ሸዋ ባኮ ከተማና በቄለም ወለጋ ሃዋ ገላን ወረዳ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፎች ተካሂደዋል።

ሰልፎቹ፤ በፖለቲካ አመለካከታቸውና የመብት ጥያቄን በማንሳታቸው የታሰሩ ሰዎች ይፈቱና መከላከያ ሰራዊት ከዩንቨርስቲ ግቢ ይውጣ የሚሉ መፈክሮች የተካተቱባቸው ነበሩ ተብሏል። ሰልፎቹ በሰላማዊ መንገድ መጠናቀቃቸውን ነዋሪዎቹ ጨምረው ተናግረዋል።ተቃውሞዎቹን በተመለከተ በመንግሥት በኩል ምላሽ ለማግኘት አልቻልንም።

ዝርዝርሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ሻምቡ ከተማ በተነሳ ተቃውሞ አንድ ሰው ሞቶ አራት ሰው ቆሰለ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:49 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG