በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ግድያ እንዲቆም የተቃዋሚ የፖለቲካ ተቃዋሚ ፓርቲዎች አሳሰቡ


ከተዘጉት ሱቆች መካከል
ከተዘጉት ሱቆች መካከል

አብዛኛው የኦሮሚያ ከተሞችና አዲስ አበባ ዙሪያ የሚገኙ ንግድ ቤቶች አስቸኳይ ጊዜ አዐዋጁን በመቃወም ዝግ ናቸው።

ግድያ እንዲቆም የተቃዋሚ የፖለቲካ ተቃዋሚ ፓርቲዎች አሳሰቡ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:17 0:00

በኢትዮጵያ በተለይ በኦሮሚያ ክልል በፀጥታ ኃይሎች እየተፈፀመ ያለው ግድያ እንዲቆም በሀገር ውስጥ የሚገኙ የተቃዋሚ የፖለቲካ ተቃዋሚ ፓርቲዎች አሳሰቡ። ለሀገሪቱ ዘላቂ መፍትሔ የሚያመጣው ብሔራዊ መግባባትና የሽግግር መንግሥት እንጂ አስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ አይደለም ብለዋል።

በሌላ በኩል የፈረንሳይ የዜና ወኪል አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ በምስል በላከው ሪፖርት አብዛኛው የኦሮሚያ ከተሞችና አዲስ አበባ ዙሪያ የሚገኙ ንግድ ቤቶች አስቸኳይ ጊዜ አዐዋጁን በመቃወም ዝግ መሆናቸውን ዘግቧል።

በፉሪና በቡራዩ የግንግድ ቤቶች መዘጋታቸውንና። የአውቶብስና የከባድ መኪኖች እንቅስቃሴ መቋረጡንም በምስሉ ላይ አሳይቷል።

የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው በሻሸመኔ፣በሜኤሶና በነጆ የሚገኙ ነዋሪዎችም የንግድ ቤቶቹ ዝግ መሆናቸንና በፀጥታ ኃይሎች እንዲከፍቱ እንደሚገደዱ ተናግረዋል። በማስገደዱ ሔደት ሱቆቻቸውና የመኝታ አገልግሎት የሚሰጡ ንግድ ቤቶች እንደተሰበሩባቸው ገለፀዋል።

በተጨማሪም በሀገሪቱ ውስጥ በተለይ ከአዲስ አበባ ውጪ ከአንዱ ቦታ ወደ አንድ ቦታ መንቀሳቀስ አቸጋሪ መሆኑን ገለፀዋል።የስልክ ኢንተርኔት አገልግሎትም በአብዛኛው የክልል ከተሞች መቋረጡን ተናግረዋል።

የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁ ኮማንድ ፖስት ዐዋጁ የወጣው በሀገሪቱ የተፈጠረውን አለመረጋጋትና ሁከት አስቁሞ ወደ ነበረበት ለመመለስ እንደሆነ መግለፁ ይታወሳል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG