በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኦሮሚያ ክልል ምዕራባዊ ዞኖች የሚገኙ ተፈናቃዮች በዐዲሱ ዓመት መመለስን ተስፋ ያደርጋሉ


በኦሮሚያ ክልል ምዕራባዊ ዞኖች የሚገኙ ተፈናቃዮች በዐዲሱ ዓመት መመለስን ተስፋ ያደርጋሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:04 0:00

በኦሮሚያ ክልል ምዕራባዊ ዞኖች የሚገኙ ተፈናቃዮች በዐዲሱ ዓመት መመለስን ተስፋ ያደርጋሉ

በኦሮሚያ ክልል ምዕራባዊ ዞኖች በነበረው የጸጥታ ስጋት ተፈናቅለው በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ አንዳንድ ተፈናቃዮች፣ በሚቀጥለው 2016 ዓ.ም. ወደቀዬአቸው ለመመለስ ተስፋ እንደሚያደርጉ ገለጹ።

አስተያየታቸውን ለአሜሪካ ድምፅ የሰጡ ተፈናቃዮች፣ በመጪው ዘመን ሁከቱ እና አለመረጋጋቱ ተወግዶላቸው በሰላም ወጥተው በሰላም የሚገቡበትና ሠርተው የሚያተርፉበት ዓመት እንዲኾንላቸው ተመኝተዋል።

በክልል ውስጥ ያለው የጸጥታ ችግር እንዲቀረፍም፣ መንግሥት እና የታጠቁ ኃይሎች ተቀራርበው በመወያየት ሰላም እንዲያወርዱ ጥሪ አቅርበዋል።

በአራቱ የወለጋ ዞኖች፣ ከግጭት የተነሳ ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ከ725ሺሕ በላይ ሰዎች፣ በአስከፊ ኹኔታ ውስጥ እንደሚኖሩ፣ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ(UN-OCHA) ከዚኽ ቀደም ገልጿል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ዘገባ ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG