በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኦሮምያና የሶማሌ ተጎራባቾች አጠቃላይ ሁኔታ


በኦሮምያና በሶማሌ ክልሎች መካከል እየታየ ያለው ግጭትና ጥቃት የብዙ ኢትዮጵያዊያንን ሕይወት በልቷል።

በኦሮምያና በሶማሌ ክልሎች መካከል እየታየ ያለው ግጭትና ጥቃት የብዙ ኢትዮጵያዊያንን ሕይወት በልቷል።

ብዙ የደካማ ገበሬዎችን፣ ከብት አርቢዎችና ነጋዴዎችን ጥሪትና ንብረት አጥፍቷል። የዜጎችን ሥነ-ልቦና፣ የሃገሪቱን ደኅንነት ተፈታትኗል።

ይህ ግጭት ለዓመታት የነበረ የአጎራባች ቀበሌዎች ድንገተኛ ግጭት ወይም የሃብት ቅርምት ወይም የውኃና የግጦሽ ሽሚያ መቆራቆስ አይደለም።

እንዲህ ዓይነት በሁለት የፌደራል አስተዳደሩ አቻ አባላትና የመንግሥቱ አካላት የሆኑ ክልሎች መካከል የተጫሩና መብረጃ አጥተው የቆዩ ትንቅንቆች፣ ሃይ ባይ ገላጋይ የሌላቸው መስለው ሰንብተዋል።

አድራጎቶቹ በሃገሪቱ ታሪክ ታይተው የማይታወቁ ከመሆናቸው ጋር ብዙ ሰው አስደንግጧል፤ ብዙ ሰው አሳዝኗል፤ አስደምሟል።

የሁለቱም ክልሎች ርዕሳነ መስተዳድር ዕሁድ፤ መስከረም 7/2007 ዓ.ም አጠገብ ላጠገብ ተቀምጠው ለጠፋው ሕይወት፣ ለፈሰሰው ደም፣ ለተጎዳው ሞራል፣ ለወደመው ንብረት ቁጥትና ኀዘናቸውን ገልፀዋል።

የኦሮምያው ፕሬዚዳንት ለማ መገርሳ የሁኔታው አዝማሚያ ለሃገሪቱ በአጠቃላይ አደገኛ መሆኑን አሳስበው ተጠቃቂ የሚባሉ ሕግ ፊት እንዲቀርቡ ጠይቀዋል።

የሶማሌው ፕሬዚዳንት አብዲ መሐመድ ዑመር “የታየው ሁሉ የኦሮሞም የሶማሌም ያልሆነ የውጭ ባሕል ነው” ብለውታል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ ከሁለቱም ክልሎች የሃገር ሽማግሌዎች ጋር ተቀምጠው መክረዋል፤ ፌደራሉ ኃይል በግጭቶቹ አካባቢዎች ገብቶ እንዲያረጋጋ ማዘዛቸውን ተናግረዋል፤ ሌሎች ወገኖች አለመግባባቶችን ከሚያባብሱ አድራጎቶች እንዲቆጠቡ አሳስበዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ሶማሊያ ውስጥ ሃርጌሣ በሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ላይ ጥቃት እየተፈፀመ መሆኑን እዚው ነዋሪ የሆኑ ስደተኞች ለቪኦኤ ገልፀዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ከፍተው ያዳምጡ።

የኦሮምያና የሶማሌ ተጎራባቾች አጠቃላይ ሁኔታ
please wait

No media source currently available

0:00 0:21:49 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG