በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ምስራቅ ወለጋ ውስጥ በመኪና አደጋ የ43 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ወረዳው አስታወቀ


የኢትዮጵያ ካርታ
የኢትዮጵያ ካርታ
ምስራቅ ወለጋ ውስጥ በመኪና አደጋ የ43 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ወረዳው አስታወቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:53 0:00

ዛሬ የካቲት 4 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ ሁለት ሰዓት አካባቢ በኦሮምያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን ጉደያ ቢላ ወረዳ ልዩ ስሙ "ኢፋ ቢያ" በተባለ ቦታ ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ 43 ሰዎች ሕወታቸው ማለፉን እና 42 ሰዎች ደግሞ ለከባድ አካል ጉዳት መዳረጋቸውን፣ የጉደያ ቢላ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ሽብሩ ፀጋዬ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

አደጋው ከሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ሻምቡ ከተማ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ የነበረ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ይሰጥ የነበረ ተሽከርካሪ ፍሬኑ በመበላሸቱና፣ መንገድ ጥሶ ገደል በመግባቱ እንደኾነ ኃላፊው ተናግረዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG