በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኦሮሚያ ክልል ሁከት በመቀስቀስ የተጠረጠሩ መታሰራቸው ተገለፀ


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

በሰሞኑ በኦሮምያ የተለያዩ አካባቢዎች ተቀስቅሶ ብዙ ህይወት ከጠፋበትና ብዙ ንብረት ከወደመበት ሁከት ጋር በተያያዘ ሆለታ ከተማና ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ውስጥ “ከመቶ በላይ ሰዎች ታስረዋል” ሲሉ ቤተሰቦችና በየአካባቢው የሚገኙ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስና ኦሮሞ ነፃነት ግንባር አባላት ገልፀዋል።

የሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን የፀጥታና አስተዳደር ፅህፈት ቤት ሰዎች መታሠራቸውን አረጋግጦ የታሠሩት ግን የድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያን በሚያወግዝ ሰልፍ ላይ በመሳተፋቸው ሳይሆን በወንጀል ድርጊት ተጠርጥረው እንደሆነ አመልክቷል።

በሌላ በኩል ደግሞ ምዕራብ ኦሮምያ ከተሞች ውስጥ በሰውም ሆነ በንብረት ላይ ጉዳት ባይደርስም የጥፋት ሙከራ ያደረጉ ሰዎች መታሠራቸውን የኦሮምያ ክልላዊ መንግሥት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ባልቻ ተናግረዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

በኦሮሚያ ክልል ሁከት በመቀስቀስ የተጠረጠሩ መታሰራቸው ተገለፀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:31 0:00


XS
SM
MD
LG