አዲስ አበባ —
በእነዚህ ሁለት ቀናት በኦሮምያ የተለያዩ አካባቢዎች የተካሄዱ ሰላማዊ ሠልፎች መነሻ ከሶማሌ ክልል የተፈናቀሉ ወገኖች ጉዳይ ቢሆንም ከአለፈው ዓመት የቀጠሉ ብሶቶችም ተንፀባርቀዋል ይላሉ አንዳንድ ተሳታፊዎች፡፡
ኢህአዴግ በወታደራዊ ኃይል የረገበን ውጥረት እንደ ቋሚና ዘላቂ ሠላም ቆጥሯል፣ የአለፈውን ዓመት ሁኔታም ረስቷል ሲሉ የተቹት ደግሞ አንድ የተቃዋሚ መሪ ናቸው፡፡
ትናንት የተቀሰቀሰው ተቃውሞና የተካሄደው ሰላማዊ ሠልፍ ዛሬም ከቀጠለባቸው የኦሮምያ ክልል ከተሞች አንዷ ሻሸመኔ ናት፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ