በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሰደድ እሳት በዩናይትድ ስቴትስ ከባድ ውድመት እያደረሰ ነው


ኦሬገን
ኦሬገን

በዩናይትድ ስቴትስ ከባድ የሰደድ እሳት ውድመት እያደረሰ እና ማኅበረሰቦችን ያለመጠጊያ ያስቀረው ሰደድ እሳት ከአቅማችን በላይ ሆኗል ሲሉ የኦሬገን ክፍለ ግዛት አስተዳዳሪ ኬት ብራውን ተናገሩ።

አስተዳዳሪዋ ትናንት ማታ ለጋዜጠኞች በሰጡት ቃል ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ተጨማሪ እርዳታ ከፌዴራል መንግሥት እንድናገኛ የከባድ አደጋ ሁኔታ እንዲያውጁልን ጠይቄያቸዋለሁ ብለዋል።

ፕሬዚዳንቱ ባለፈው ሳምንት ለኦሬገን የአስቸኳይ ሁኔታ አውጀዋል። ኦሬገን ውስጥ እስካሁን በቃጠሎው አሥር ሰዎች መሞታቸው መረጋገጡን ያልተገኙ ሃያ ሁለት ሰዎች መኖራቸውን የክፍለ ሃገርዋ የአጣዳፊ አደጋ አስተዳደር አስታውቋል።

ሰደድ እሳቱ እየነደደ ባለባቸው በኦሬገን ፥ ዋሽንግተን እና ካሊፎርንያ ሰላሳ አምስት ሰዎች ሞተዋል፥ ከአንድ ሚሊዮን ሄክታር በላይ መሬት አውድሟል።

ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ
ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ

ስለሰደድ እሳቱ ሰደድ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕና ዲሞክራቱ ተፎካካሪያቸው ጆ ባይደን የቃጠሎውን መነሾ እጅግ በተራራቀ መንገድ ገልጸውታል።

ትናንት ሰኞ ካሊፎርኒያን የጎበኙት ትረምፕ ሰደድ እሳቱ ብዙ ቦታ እየተነሳና እየተጠናከረ የመጣው በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ነው የሚለውን አመለካከት አጣጥለው ክፍለ ግዛቶቹን "ይልቁን የደን አያያዛችሁን አሻሽሉ" ሲሉ ተናግረዋል።

ዛፍ ሲወድቅ ጥቂት ቆይቶ ይደርቃል፥ ክብሪት እንጨት ማለት ነው፤ ቅጠሉም ውድቆ ሲደርቅ እሳት ላይ የተጨመረ ነዳጅ ማለት ነው ብለዋል።

ጆ ባይደን
ጆ ባይደን

ጆ ባይደን በሚኖሩበት በዴላዌር በሰጡት ቃል ፕሬዚዳንቱ አየር ንብረት ለውጥ የሚባል የለም ማለታቸው ሰደድ እሳቱን አልፈጠረውም። ነገር ግን አስተዳደሩ ላይ ለሁለተኛ ጊዜ ከተቀመጡ አሁን የምናየው መዓት ይባባሳል ብዙ ውድመት ብዙ የህይወት ጣፋት ያስከትላል፤ ከተመርጥኩ የዓለም የአየር ግለት ለመዋጋት ፈጣን እርምጃ እወስዳለሁ ብለዋል። በዩናይትድ ስቴትስ ምዕራባዊ ክፍለ ግዛቶቹዋ ደኖችን እያጋየ ስላለው እና ቢያንስ የሰላሳ አምስት ሰዎች ህይወት የጠፋበትን ሰደድ እሳት በተመለከተ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕና ዲሞክራቱ ተፎካካሪያቸው ጆ ባይደን የቃጠሎውን መነሾ እጅግ በተራራቀ መንገድ ገልጸውታል።

XS
SM
MD
LG