ዋሽንግተን ዲሲ —
በኢትዮጵያ ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ከተጀመረ ከሁለት ዓመት በላይ ሆኖቷል። ይህ ተቃውሞም ግድያ፣ አካል መጉደል፣ ንብረት መውደም እስርና በአጠቃላይ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ሀገሪቱ ላይ ፈጥሯል። ከዚህ በኋላ ለ18 ቀናት በሩን ለስብሰባ ዘግቶ የነበረው የገዢው ፓርቲ ኢሕዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ስብሰባውን አጠናቆ ባወጣው መግለጫ ፤ በአመራር ድክመት የተፈጠሩትን አደጋዎችና ሥጋቶች ለመቅረፍ በሚያስችል መግባባትና ስምምነት ግመገማውን ማጠናቀቁ አስታውቋል።
በሀገሪቱ የተቃውሞ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ የሚታወቁት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስና ሰማያዊው ፓርቲ “መግለጫው ምንም አዲስ ነገር የለውም የተለመደው አዘናግቶ መግዢያና አምባገነንነትን ማስቀጠያ ነው” ብለውታል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ