በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያው ምርጫና የተቃዋሚዎቹ የዛሬ አቋም



የአዲስ አበባ ምርጫ ተሳታፊዎች
የአዲስ አበባ ምርጫ ተሳታፊዎች

"ፍትሐዊ ምርጫ ቀልድ ነበር" - ኢፍዴኃግ

በበርካታ ጉዳዮች ላይ ስምምነት የሌላቸው 65 ተቃዋሚ ፓርቲዎች በምርጫው ከተደረሰባቸው ሰባሪ ሽንፈት ለማገገም እየተፍጨረጨሩ እንደሆነ ይታያል፡፡ ብዙዎቹ ግን በአንድ ጉዳይ ላይ ወደአንድ ሠልፍ እየገቡ ይመስላሉ - በምርጫው ውጤት፡፡

ከ547ቱ የፓርላማ መቀመጫዎች አሥር ከመቶ የማይሞሉትን የተቃዋሚ የሚባሉ መቀመጫዎች በብዙ መንገድ ነው የሚቀራመቷቸው፡፡

የስድስት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጥምረቱ የኢትዮጵያ የፍትሕና የዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ግንባር አዲስ ምርጫ መካሄድ አለበት የሚለውን አቋም ተቀላቅሏል፡፡ ይህንን አቋም የሚያራምዱት ወገኖች ገዥው ፓርቲ ምርጫውን አጭበርብሯል፤ ዕጩዎቻቸውና ድምፅ ሰጭዎች ተዋክበዋል፤ እንዲሸማቀቁ ተደርገዋል ባይ ናቸው፡፡

የመንግሥት ባለሥልጣናቱ ደግሞ ተቃዋሚዎች ቅሬታቸውን መናገር እንደሚችሉ ቢናገሩም ድጋሚ ምርጫ የሚባል ነገር ግን የሚታሰብ ነገር እንዳልሆነ ያሣስባሉ፡፡

በረከት ስሞኦን
በረከት ስሞኦን

"ሕዝቡ የተናገረ ይመስለኛል - ብለዋል የኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ሚኒስትሩ በረከት ስምዖን - በዚህ ከፍተኛ ድል ውስጥ የሚያወዛግብ ነገር የለም፤ ውዝግብ ካለም የሕዝብን አመኔታ ባጡት ዘንድ ነው ያለው፡፡"

ይሁን እንጂ ደርሰዋል የሚባሉ ችግሮችን በገሃድ የሚያሣዩ ቁጥራቸው የበዛ ማስረጃዎች በእጃቸው እንደሚገኙ ታዛቢዎቻቸው ከብዙ የምርጫ ጣቢያዎች መባረራቸውን እየተናገሩ ነው፡፡ ቀድሞውንም ቢሆን ወደምርጫው ፉክክር የገቡት መንግሥት ነፃና ፍትሐዊ ምርጫ አካሂዳለሁ ብሎ ስለነበረ ቃሉን ይጠብቃል በሚል እምነት እንደነበረ አመልክተዋል፡፡ "ያ የፍትሐዊ ምርጫ ቃል ግን ቀልድ ሆኖ ቀረ" ብለዋል የፍትሕና የዴሞክራሲ ኃይሎች ግንባር ዋና ፀሐፊ ገረሱ ጋሳ፡፡- "የተመቻቸ ሁኔታ እንፈጥራለን ብለው ነበር፡፡ ነፃ ምርጫ፣ ፍትሐዊ ምርጫ ብለው ነበር፡፡ ያ ግን አልሆነም፡፡ አሁን እንደገባን እየቀለዱ ነው፡፡" ሲሉም አክለዋል፡፡

የምርጫው ሂደት አያያዝና አሠራር እራሱ በተፈጥሮው ለተቃዋሚ ፓርቲዎች የማይመች፣ ለገዥው ፓርቲ የሚያዳላ እንዲሆን ተደርጎ የተዋቀረ እንደሆነ ይናገራሉ ዋና ፀሐፊው፡፡

ትልልቆቹ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ናቸው የሚባሉት መድረክና የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ፓርቲ አዲስ ምርጫ እንዲደረግ ባለፈው ሣምንት ጠይቀዋል፡፡ በፓርላማው ውስጥ በንቃት ይሣተፍ የነበረው የኢትዮጵያዊያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲም ቢሆን መንግሥትን አካሂዷል በሚላቸው የሰፉ ችግሮች ሲከስ ተደምጧል፡፡ ሌላ ዙር ምርጫ እንዲካሄድ ከመጠየቅ ግን ተቆጥቧል፡፡

XS
SM
MD
LG