ዋሽንግተን ዲሲ —
በሣምንቱ መጨረሻ በአዲስ አበባ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አዳራሽ የሚያደርጉትን ውይይት ያጠናቀቁት ገዢው ኢሕአዴግና ዐስራ ስድሥት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ዋናውን ድርድር ለመጀመር ወስነዋል።
የፀረ ሽብር ሕጉን ጨምሮ በተቃዋሚዎች በቀረቡ ልዩ ልዩ አዋጆች ላይ ለመደራደር የተስማማው ኢሕአዴግ የፖለቲካና የሕሊና እሥረኞች በሚል ርዕስ የቀረበውን የመነጋገሪያ አጀንዳ ግን እንደማይቀበለው አስታውቋል።
በዚህ ድርድር የማይካፈሉት የበርካት ኣተቃዋሚ ፓርቲዎች ጥምረት መድረክና ሰማያዊ ፓርቲ ገዥው ፓርቲ አባላቶቻችንና አመራራችንን አስሮ፤ እንደራደር ማለት፤ ሀቀኛ የፖለቲካ መንገድ አይደለም ይላሉ። በድርድሩና በአጀንዳዎቹ ዙሪያ ጽዮን ግርማ የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ ምክትል ሊ/መንበር አቶ ሙላቱ ገመቹና፤ የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ የሽዋስ አሰፋን አነጋግራለች።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ