በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የከንቲባ አዳነች አበቤ ሪፖርትና የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች ተቃውሞ


የከንቲባ አዳነች አበቤ ሪፖርትና የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች ተቃውሞ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:00 0:00

የከንቲባ አዳነች አበቤ ሪፖርትና የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች ተቃውሞ

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ከአንዳንድ ክልሎች ወደ አዲስ አበባ የሚደረገው ፍልሰት በሕዝብ የተመረጠን መንግሥት በአመጽ ለመጣልና በኃይል ሥልጣን ለመቆጣጠር ያለመ ነው ሲሉ ከንቲባ አዳነች አበቤ ገለፁ፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር በከተማዋ “በፍልሰት” በማለት በተጠቀሙት አገላለፅ “ከ60 በመቶ በላይ የሚሆኑት አብዛኞቹ ሰዎች ከአማራ ክልል የሚመጡ ናቸው” ብለዋል፡፡

እናት፤ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ)ና ኢህአፓን የመሳሰሉ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች የከንቲባዋ ሪፖርት የሰዎችን የመንቀሳቀስ ሰብአዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ሕገ መንግሥታዊ መብቶችን የሚጋፋ፣ በሕዝቦች መካከል ልዩነትንና ጥላቻን የሚያባብስ፤ ከዚህ ቀደም ለተፈጸሙ ወንጀሎች ሽፋን የሚሰጥ ነው ሲሉ ተችተዋል፡፡

የከንቲባዋን ሪፖርት “ሀገረ መንግሥቱን አደጋ ላይ የሚጥል የዓለም አቀፍ ወንጀል ጥሪ ነው ሲል” የተቸው የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ በበኩሉ መንግሥት ከንቲባዋን ከሥልጣናቸው አንስቶ በሕግ ተጠያቂ ሊያደርጋቸው ይገባል ሲል መግለጫ አውጥቷል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG