በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሶማሌ ክልል የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች መግለጫ


በሶማሌ ክልል የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች
በሶማሌ ክልል የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች

በሶማሌ ክልል የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች በትናንትናው ዕለት በጂጂጋ ከተማ ባካሄዱት ስብሰባ፣ ህወሓት በሀገር መከላከያ ሰራዊት ላይ ፈጽሞታል ያሉትን ጥቃት አውግዘው፣ ባለፉት 27 ዓመታት በሶማሌ ክልል ጅምላ ጭፍጨፋ ሲፈጽም ነበር ያሉት የህወሓት ቡድን ለህግ እንዲቀርብም ጠይቀዋል።

የክልላቸውን ሰላምም በጋራ ለመጠበቅ ተስማምተዋል። የክልሉ ዋነኛ ተፎካካሪ ፓርቲ ኦብነግ ከ6ቱ ፓርቲዎች ጋር በጋራ ካወጣው አቋም መግለጫ ባሻገር፣ በድርጅቱ የትዊተርና የፌስቡክ ገጽ የህወሃትን ድርጊት የሚኮንን፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የጀመሩት የለውጥ መንገድ ተስፋ የሚጣልበት እንደሆነ የሚገልጽና ጦርነትን የሚያወግዝ መግለጫ አውጥቷል።

የክልል መንግሥታትም ህወሓትን የሚያወግዝ መግለጫ አውጥተዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡

በሶማሌ ክልል የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች መግለጫ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:40 0:00


XS
SM
MD
LG