በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በእስር ላይ ያሉ የተቃዋሚ መሪዎች “ተቀባይነት የሌላቸው” ያሏቸው ማስረጃዎች ይነሱልን ጥያቄ


ፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
ፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:19 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ተኛው ወንጀል ችሎት በሽብር ከተከሰሱት የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች መካከል አብዛኛቹ በአቃቤ ሕግ ማስረጃ ላይ ያቀረቡትን መቃወሚያ ውድቅ አደረገ።

ካሁን ቀደም በዋለው ችሎት ሰባት ተከሳሾች አቃቤ ሕግ ያቀረባቸዉን የክስ ማስረጃዎች ተቃውመዉ ፍርድ ቤቱ ከመዝገቡ እንዲያስወጣላቸዉ በጠበቃቸው አማካይነት ጠይቀው ነበር።

የቀድሞ የአንድነት ፓርቲ አመራር አባላት ሃብታሙ አያሌውና ዳንኤል ሺበሺ፣ የአረና ትግራይ አመራር አባል አብረሃ ደስታ፣ የሰማያዊ ፓርቲ አመራር አባል የሽዋስ አሰፋ፣ ዮናታን ወልዴ፥ ባህሩ ደጉና ዘላለም ወርቅ አገኘሁን በመወከል፣ ጠበቃቸው ተማም አባ ቡልጉ ተቀባይነት የሌለባቸዉ ያሉዋቸዉ ማስረጃዎች ከክስ መዝገቡ እንዲወጡ ለፍርድ ቤቱ አቤት ብለዉ ነበር።

ፍርድ ቤቱ ግን ጉዳዮን እንደመረመረው የተከሳሾቹን ጥያቄ የሚደግፍ የሕግ ድንጋጌ እንደሌለ ”በአቃቤ ሕግ የቀረቡት ማስረጃዎች ሁሉ በወንጀል ሕጉም ሆነ በጸረ ሽብር ሕጉ የተደገፉ ናቸው፤” የሚል ውሳኔ በመስጠት አቤቱታቸውን ውድቅ አድርጎ ጉዳዮን ለሌላ ጊዜ ቀጥሯል።

XS
SM
MD
LG