አዲስ አበባ —
ኦህዴድ ዛሬ ያካሄደው የኃላፊነት ሽግሽግ የቀጠዩን የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር ማንነት ያመላከተ እንደሆነ የሚገልፁ አስተያየቶች እየተሰጡ ነው፡፡
የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ ዛሬ ባካሄደው ስብሰባ ዶ/ር አብይ አህመድን ሊቀመንበር፣ ሊቀመንበር የነበሩትን አቶ ለማ መገርሳን ደግሞ ምክትል አድርጎ ነው የመረጠው፡፡
ኦህዴድ ራሱ ግን ዶ/ር አብይ የኢህአዴግ ሊቀመንበርና የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስተር እንዲሆኑ በዕጩነት ለማቅረብ ወሳኔ ላይ ስለመድረሱ ከመናገር ተቆጥቧል፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ