በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሶሪያ የደረሰው የኬሚካል ጥቃት በክሎሪን ጋዝ የተፈፀመ መሆኑ ተገለፀ

ባለፈው የካቲት ሶሪያ ውስጥ የደረሰው የኬሚካል ጥቃት በክሎሪን ጋዝ የተፈፀመ ነበር የሚል ድምዳሜ ላይ መድረሣቸውን የዓለምቀፉ የኬሚካል ጦር መሣሪያዎች እገዳ ድርጅት መርማሪዎች አስታወቁ።

ባለፈው የካቲት ሶሪያ ውስጥ የደረሰው የኬሚካል ጥቃት በክሎሪን ጋዝ የተፈፀመ ነበር የሚል ድምዳሜ ላይ መድረሣቸውን የዓለምቀፉ የኬሚካል ጦር መሣሪያዎች እገዳ ድርጅት መርማሪዎች አስታወቁ።

ቡድኑ ምርመራውን ያካሄደው ከጤና ሠራተኞችና ከእማኞች የምሥክርነት ቃሎችን በመሰብሰብ እንዲሁም ጥቃቱ ከተፈፀመበት ከኢድሊብ ክፍለሃገር ሳራቄብ አካባቢ ናሙናዎችን በመውሰድ እንደሆነ ተገልጿል።

በወቅቱ ጥቃቱ የተፈፀመባቸው ሲቪሎች የመተንፈስ ችግርና በልብሶቻቸው ላይ የክሎሪን ሽታን ጨምሮ ለክሎሪን ጋዝ የመጋለጥ ምልክት ያሳዩ እንደነበር የሕክምና ባለሙያዎች ማረጋገጣቸውን ቡድኑ አስታውቋል።

ጥቃቱን ያደረሱት የሶሪያው ፕሬዚዳንት ባሻር አል አሳድ ኃይሎች ናቸው ሲሉ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ኒኪ ሄሊ መክሰሳቸው ይታወሳል።

የሶሪያ መንግሥት ግን ኬሚካል የጦር መሣሪያ አለመጠቀሙን በተደጋጋሚ ሲያስተባብል ይሰማል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG