በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኦነግ ከትጥቅ ትግል ወደ ሰላማዊ ትግል ለመግባት ተስማማ


ኦነግ ከትጥቅ ትግል ወደ ሰላማዊ ትግል ለመግባት የሚያስችለውን ሥምምነት ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ተፈራርሟል፡፡

ኦነግ ከትጥቅ ትግል ወደ ሰላማዊ ትግል ለመግባት የሚያስችለውን ሥምምነት ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ተፈራርሟል፡፡

የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዚዳንት አቶ ለማ መገርሳና የኢፌዴሪ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ትናንት አስመራ ውስጥ በኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ሊቀ መንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ከሚመራው ልዑክ ጋር የእርቅ ውይይት ተካሂዷል። በውይይቱ መድረክም የተለያዩ ጉዳዮች ተነስተው ምክክር ተደርጎባቸዋል፡፡

በዚህም ኦነግ ለበርካታ ዓመታት ሲያካሄድ የቆየውን የትጥቅ ትግል በማቆም በሀገሪቱ በተፈጠረው መልካም አጋጣሚ ትግሉን በሰላማዊ መንገድ ለመቀጠል ከሥምምነት ላይ ደርሷል።

በቅርቡ በውጭ አገር የሚኖሩ በርካታ የፖለቲካ ፓርቲዎች ወደ ሀገሪቱ መግባታቸው ይታወሳል፡፡

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG