በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን ከኦነግ ክንፍ ጋር ለመወያየት አስመራ ገቡ


በከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ ባለሥልጣናት የተመራ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን አሁንም ድረስ ኤርትራ ከሚገኝ ከአንድ የተቃዋሚ ቡድን ጋር ለመወያየት በዛሬው ዕለት ወደ አሥመራ አቅንቷል፡፡

በከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ ባለሥልጣናት የተመራ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን አሁንም ድረስ ኤርትራ ከሚገኝ ከአንድ የተቃዋሚ ቡድን ጋር ለመወያየት በዛሬው ዕለት ወደ አሥመራ አቅንቷል፡፡

በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወርቅነህ ገበየሁ እና በኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ለማ መገርሳ የተመራው ይህ የልዑካን ቡድን ከኦሮሞ ነጻነት ግንባር ክንፍ ጋር ለመወያየት ነው ወደ ኤርትራ ያመራው፡፡

ማለዳ ላይ አስመራ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ በኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኡስማን ሳልኽ እና በሌሎች ከፍተኛ የሀገሪቱ ባለሰልጣናት አቀባበል የተደረገለት የልዑካን ቡድን ከኦነግ መሪ አቶ ዳወድ ኢብሳ ጋር ተገናኝቶ ዛሬ ይወያያሉ ተብሎም ይጠበቃል፡፡

የልዑካን ቡድኑ ጉዞ የኢትዮጵያ መንግስት የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋት በውጭ ሃገር የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሀገር ውስጥ ገብተው በሰላማዊ መንገድ እንዲንቀሳቀሱ ከዚህ ቀደም ካቀረበው ጥሪ ጋር በተያያዘ ነው ተብሏል፡፡

ጥሪውን ተከትሎም በውጭ ሀገር የሚገኙ በርካታ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ወደ ሀገር ውስጥ መግባታቸው ይታወቃል፡፡ ከዚህ ቀደም እንደ ኦነግ ሁሉ በኤርትራ ይንቀሳቀስ የነበረው የአርበኞች ግንቦት ሰባት አመራሮች በመጭው አንድ ወር ጊዜ ውስጥ ወደ ሀገር ተመልሰው በፖለቲካው ለመንቀሳቀስ ያላቸውን ዕቅድ ሰሞኑን ይፋ ማድረጋቸውም ተዘግቧል፡፡

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG