በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኦብነግ እሥረኞች መፈታት ጉዳይና የግንባሩ ውዝግብ


የኢትዮጵያ መንግሥት አሥሯቸው የነበሩ ወደ አንድ ሺህ የሚጠጉ የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ አውጭ ግንባር አባላትን ለቅቋል ሲሉ ከመንግሥት ጋር ስምምነት የተፈራረመው አንጃ መሪ አቶ ሣላሁዲን ማኦ አስታወቁ፡፡

እሥረኞቹ የተለቀቁት ባለፈው ጥቅምት ወር ባደረጉት ስምምነት መሠረት መሆኑንም ሣላሁዲን ማኦ አመልክተዋል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ስምምነቱ በአንድ የኢትዮጵያ መንግሥት ከአንድ ግለሰብ ጋር ያደረገውና በእርሣቸው ወገን ተቀባይነት የሌለው መሆኑን የኦብነግ የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ አባልና የኢትዮጵያ ጉዳይ ኃላፊ አቶ ሃሰን አብዱላሂ ተናግረዋል፡፡

ሁለቱንም የግንባሩን ሰዎች ሰሎሞን አባተ አነጋግሮ የሚከተለውን ዘገባ አዘጋጅቷል፡፡ ዝርዝሩን ያዳምጡ

XS
SM
MD
LG